Good Will Construction Materials Supply PLC

Good Will Construction Materials Supply PLC Good will construction materials supply Plc creating lasting partnership & trust with our customers.

Being instrumental in the image building of the country by providing world class, durable and matched quality product to the market .

27/10/2022
16/06/2022
“ፍቅርም እንደዚህ ነው፤ እግዚአብሔር እርሱ ራሱ እንደ ወደደን ስለ ኃጢአታችንም ማስተስሪያ ይሆን ዘንድ ልጁን እንደ ላከ እንጂ እኛ እግዚአብሔርን እንደ ወደድነው አይደለም።” 1ኛ ዮሐንስ 4...
22/04/2022

“ፍቅርም እንደዚህ ነው፤ እግዚአብሔር እርሱ ራሱ እንደ ወደደን ስለ ኃጢአታችንም ማስተስሪያ ይሆን ዘንድ ልጁን እንደ ላከ እንጂ እኛ እግዚአብሔርን እንደ ወደድነው አይደለም።” 1ኛ ዮሐንስ 4፥10

23/02/2022

አዲሱን የኮንስትራክሽን ብቃት ማረጋገጫና ምዝገባ መመሪያ ዋና ዋና ነጥቦች
✍️✍️✍️✍️✍️✍️✍️✍️✍️
የኮንስትራክሽን ብቃት ማረጋገጫና ምዝገባ መመሪያ ቁጥር 648/2013 በቅርቡ ፀድቆ ስራ ላይ መዋሉ ይታወቃል:: መመሪያው ቀደም ሲል በስራ ላይ የነበሩት የምዝገባና ሰርተፍኬት መመሪያዎች ማለትም መመሪያ19/2005 እና መመሪያ 22/2005 ክፍተቶችን በማሻሻል ተክቶ የወጣ ነው፡፡ ስምንት ክፍሎች ያሉት መመሪያው ጠቅላላ ድንጋጌዎችን፣ የኮንስትራክሽን ድርጅት፣ ባለሙያ ፕሮጀክት ብቃት ማረጋገጫና ምዝገባ ስነ-ስርዓትን ያመላክታል፡፡ እንዲሁም የኮንስትራክሽን ባለሙያዎች፣ ድርጅቶችና ፕሮጀክቶች ምድብንም አካቷል፡፡ በተጨማሪም የኮንስትራክሽን ባለሙያዎችና ሙያተኞችን፣ ስራ ተቋራጮችን አማካሪዎችን እና የኮንስትራክሽን ፕሮጀክቶችን ብቃት ማረጋገጫና ምዝገባ ሥርዓትንም አመላክቷል፡፡

መመሪያው ደረጃን፣ የፕሮጀክት መጠን እና የሰው ኃይልን መስፈርቶች አስገዳጅ ጉዳዮችንም ፣ ስለቅሬታ አቀራረብ፣ እንዲሁም ኃላፊነትንና ተጠያቂነትንም የተመለከቱ ጉዳዮችን አካቶ የያዘ ነው::

ይህ መመሪያ የተፈፃሚነት ወሰኑ በኮንስትራክሽን ስራዎች እና አገልግሎቶች ላይ በሚሰማሩ የኮንስትራክሽን ባለሙያዎች ድርጅቶች እና ፕሮጀክቶች ላይ ተፈጻሚ የሚሆን መሆኑን መመሪያው ይገልጻል፡፡

እንዲሁም ማንኛውንም የሀገር ውስጥ ወይም የውጭ ሀገር ዜግነት ያለው የኮንስትራክሽን ባለሙያ ፤ ሙያተኛና ድርጅት የብቃት ማረጋገጫ ወይም ምዝገባ የምስክር ወረቀት ሊኖራቸው እንደሚገባ ያትታል፡፡
የብቃት ማረጋገጫ ወይም የምዝገባ የምስክር ወረቀት ሊይዛቸው የሚገቡ ዝርዝሮችን ምን ምን ናቸው የሚለው በመመሪያው የተገለጸ ሲሆን
✍️ የአመልካች ሙሉ ስም ወይም የድርጅት ስም፣
✍️የባለሙያ ምዝገባ ወይም ለብቃት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት ከሆነ የባለሙያውን የሙያ
አይነት፣ ደረጃና የምዝገባ ቁጥር እንዲሁም ምስክር ወረቀቱ የስራ ተቋራጭነት
/የአማካሪነት ብቃት ማረጋገጫ ከሆነ ምድቡን ፣ ደረጃውን እና የምዝገባ ቁጥሩን
✍️ የመጀመሪያ ምዝገባ የተደረገበት ቀን እና
✍️ በየጊዜው የሚደረግ የእድሳት ምዝገባ ቀን ማካተት ይኖርበታል፡፡ ሲል ይገልጻል፡፡
መመሪያው ተግባራዊ ከመደረጉ በፊት የብቃት ማረጋገጫ፣ የምዝገባ ምስክር ወረቀት የተሰጣቸው ባለሙያዎች መመሪያ 648/2013 ተግባራዊ ከተደረገ በኋላ ባሉት ሁለት አመታት ውስጥ በዚህ መመሪያ መሰረት በድጋሚ ማውጣት እንዳለባቸውም ይጠቅሳል፡፡
እንዲሁም መመሪያው ተግባራዊ ከመደረጉ በፊት የብቃት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት የተሰጣቸው ድርጅቶች ያሉበትን ደረጃ ለማስጠበቅ መመሪያው ተግባራዊ ከተደረገ በኋላ ባሉት ሶስት 3 ዓመታት ውስጥ ወደዚህ መስፈርት መምጣት የሚኖርባቸው ሲሆን ይህን ማሟላት ያልቻሉ ድርጅቶች በዚህ መመሪያ በተጠቀሰው መስፈርት መሰረት የሚመጡ ናቸው፡፡ የደረጃ ምስክር ወረቀት እንዲሰጣቸው እንደሚደረግ ይገልጻል፡፡

ስለ ብቃት ማረጋገጫ እና ምዝገባ ምስክር ወረቀት ደረጃ እድገት መመሪያው በተመለከተ ማንኛውም ሙያተኛ የደረጃ እድገት ማድረግ በሚፈልግበት ጊዜ እድገት ለሚደረግበት ደረጃ ከሚጠየቁ መስፈርቶች በተጨማሪ ለደረጃው ብቁ መሆኑን የሚያረጋግጥ የብቃት ምዘና ማቅረብ እንደሚኖርበት ይገልጻል፡፡

የኮንስትራክሽን ባለሙያ እና የድርጅት የብቃት ማረጋገጫ /የምዝገባ የምስክር ወረቀት የሚታገድባቸው ምክንያቶችን እያንዳንዳቸው በዝርዝር በመመሪያው ይገኛሉ፡፡

ምትክ የባለሙያ ብቃት ማረጋገጫና ምዝገባ ምስክር ወረቀት ስለመስጠት
የባለሙያ የብቃት ማረጋገጫ ወይም ምዝገባ ምስክር ወረቀት የጠፋ ከሆነ ምትክ የሚሰጠው አመልካቹ የምስክር ወረቀቱ ስለመጥፋቱ በፖሊስ አስመስክሮ መረጃ ሲያቀርብ መሆኑን የሚገልጻው መመሪያው እንዲሁም የተበላሸ ምስክር ወረቀት ምትክ የሚሰጠው የተበላሸው የምስክር ወረቀት ተመላሽ ሲደረግ ብቻ መሆኑን ይገልጻል፡፡
በተጨማሪም የኮንስትራክሽን ባለሙያዎች ድርጅቶችና ፕሮጀክቶች ምድብ የሚከተሉት መሆናቸውን መመሪያው ይገልፃል፡፡
በዚሁ መሰረትም አነስተኛ ባለሙያ፣ መለስተኛ ባለሙያ እንዲሁም ከፍተኛ ባለሙያ በሚል ይመደባሉ፡፡ በአነስተና ባለሙያዎች ስር ደረጃ አንድ እና ደረጃ ሁለት፣ በመለስተኛ ስር ደግሞ ደረጃ አንድ እና ደረጃ አራት በሚል መመሪያው ይገልፃል::

በከፍተኛ ባለሙያዎች ስር ደግሞ ምሩቅ ባለሙያ፣ ፕሮፌሽናል ባለሙያ እና ፕራክቲሲንግ ፕሮፌሽናል ባለሙያ ተብለው ይመደባሉ፡፡
የቀድሞ ስርዓተ ትምህርት ከዲግሪ በታች የነበሩት የትምህርት ደረጃዎች እና ከውጭ ሀገራት የተገኙ የት/ት ማስረጃዎች ከአዲሱ ስርዓተ ትምህርት ጋር ያላቸው አቻነት ስልጣን ባለው አካል እንደሚወሰን ይገልጻል፡፡
ከደረጃ 1-4 ያሉ አነስተኛ እና መለስተኛ ሙያተኞች ምስክር ወረቀት የሚሰጠው የብቃት ምዘና ማረጋገጫ ወስደው ላለፉት ሙያተኞች ብቻ መሆኑንና የመጀመሪያ ዲግሪና ከዚያ በላይ የትምህርት ደረጃ ያላቸው ከፍተኛ ባለሙያዎች የብቃት ማረጋገጫ ምዘና መስጠት ከሚጀምርበት ቀን ጀምሮ ምስክር ወረቀት ለማግኘት የብቃት ምዘና ማረጋገጫ ማቅረብ ግዴታ ይሆናል በሚል ተገልፆል፡፡፡፡
መመሪው የስራ ተቋራጮችን ምድብ የሚከተሉት መሆናቸውን ይገልፃል
✍️ ጠቅላላ ስራ ተቋራጭ
✍️ የህንጻ ስራ ተቋራጭ
✍️ የመንገድ ስራ ተቋራጭ
✍️ ልዩ ስራ ተቋራጭ
በልዩ ስራ ተቋራጭ የሚካተቱት የፕሬቴሽኒንግ፣ የፖስትቴንሺኒንግ፣ የመሬት ገጽታ ማስዋብ ስራዎች፣ የመሰረት ስራዎች የግንባታ ማጠናቀቅ ስራ፣ የግንባታ ቦታ ማጽዳትና ማዘጋጀት፣ የመንገድ ላይ የትራፊክ ደህንነት መቆጣጠሪያ ምልክት ስራዎች፣ የአልሙኒየም በርና መስኮት መገጣጠም ስራዎች የቀለም ቅብና ማስዋብ ስራዎች የእንጨትና ብረታ ብረት ስራዎች፣ በህንጻ ውስጥ የቦንቧና የሳኒተሪ መስመር ዝርጋታ ስራዎች ተጠቅሰዋል፡፡

ስለአማካሪ ምድብ በተመለከተም የሚመዘገቡ አማካሪዎች እንደ ስራ ምርጫቸው ሆኖ የሚከተሉት ይሆናሉ፡፡
✍️የህንጻ አማካሪ
✍️የአርክቴክቶች አማካሪ
✍️የመሃንዲሶች አማካሪ
✍️የኮንስትራክሽን ማኔጅመንት አማካሪ
✍️የከተማ ፕላን ስራዎች አማካሪ
✍️ልዩ አማካሪ የሚባሉ መሆናቸውን ይገልጻል፡፡
የኮንስትራክሽን ባለሙያዎችና ሙያተኞች ብቃት ማረጋገጫና ምዝገባ ወረቀት ለማውጣት የሚያስፈልጋቸውን መስፈርትም ያትታል፡፡
የባለሙያ እና የሙያተኞች ብቃት ማረጋገጫና ምዝገባ
ስለኮንስትራክሽን ባለሙያዎችና ሙያተኞች ብቃት ማረጋገጫና ምዝገባ አሰጣጥ አፈጻጸም
ስለአነስተኛ ሙያተኞች ብቃት ማረጋገጫና ምዝገባ
ስለ መለስተኛ ባለሙያ ብቃት ማረጋገጫና ምዝገባ
ስለ ከፍተኛ ባለሙያ ብቃት ማረጋገጫና ምዝገባ ይዘረዝራል፡፡ መመሪያ 648/2013 ከሚጠቅሳቸው ነጥቦች በጥቂቱ ከላይ የተዘረዘሩት ሲሆኑ በተጨማሪ በመጨረሻው የመመሪያው ክፍል ልዩ ልዩ ድንጋጌዎች በሚል የተቀመጡ ነጥቦች ይገኙበታል፡፡
በልዩ ልዩ ድንጋጌ የተጠቀሱት
ቅሬታ ፡- ማንኛውም ተመዝጋቢ በዚህ መመሪያ መሰረት በተሰጡ የብቃት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት እና ምዝገባ ላይ አገልግሎቱ በተሰጠ 3 ቀን ውስጥ በተቋሙ ቅሬታ ማስተናገጃ ስራ ክፍል የማቅረብ መብት እንዳለው ይጠቀሳል፡፡ መዝጋቢውም በቀረበው ቅሬታ ማመልከቻዎች ላይ ውሳኔ እንደሚሰጥ አስፈላጊ እርምጃም እንደሚወስድ ይጠቅሳል፡፡
በልዩ ድንጋጌዎች ሥር ከተቀመጠው ውስጥ ተጠያቂነት ሌላው ነጥብ ሲሆን ማንኛውም ተመዝጋቢ ከመመሪያ ውጪ የብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት እና ምዝገባ አገልግሎት ማግኘቱ ከተረጋገጠ የአገልግሎቱ መሰረዝ እንደተጠበቀ ሆኖ አግባብ ባለው በፍትሃብሄርና በወንጀል ህግ የሚጠየቅ እንደሚሆን ይገልጻል፡፡

በተጨማሪ በልዩ ድንጋጌ ላይ ስለአገልግሎት ክፍያ ስለባለሙያና የመሳሪያዎች የመተካካት አሰራር ይደነግጋል፡፡

ይህ የምዝገባ መመሪያ ከመጋቢት 2013 ዓ.ም ጀምሮ ተፈጻሚ የሆነ መመሪያ ሲሆን የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ባለስልጣንም መመሪያውን ወደ ስራ እንዲገባ ለማድረግ የተለያዩ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናዎችና ከዘርፉ ባለድርሻ አካላት ጋር በመመሪያው ዙሪያ ውይይት በማድረግ ወደ ስራ ገብቷል፡፡ በመሆኑም ተቋሙ በሚሰጣቸው የምዝገባ ስራዎች ላይ ከሰኔ 2013 ጀምሮ መመሪያው ተግባራዊ እየተደረገ መሆኑ ይታወቃል፡፡

መረጃው፡- የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ባለስልጣን
=====//=========

Happy New Year!!!
07/09/2021

Happy New Year!!!

Civil  Engineering information ፦
09/02/2021

Civil Engineering information ፦

Our sanitary ware products Gold Dragon brand made with high quality material and polished with super fine glaze which gi...
02/02/2021

Our sanitary ware products Gold Dragon brand made with high quality material and polished with super fine glaze which gives scratch-resistant, long lasting and better durability as compare to the existing products in the market.
Our sanitary accessories ware products such as basin mixer, shower mixer and other bathroom accessories are made with full brass material with best quality chrome which gives ever-lasting and make sure it is always clean.
All kind of size by any quantity can be supply to your project according to your requirements.
Meet our team :
Your satisfaction is our forever gold.

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Good Will Construction Materials Supply PLC posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Good Will Construction Materials Supply PLC:

Share