ማሌ ዓርና አክሲዮን ማኅበር - Maalle Arna Share Company

  • Home
  • Ethiopia
  • Malle
  • ማሌ ዓርና አክሲዮን ማኅበር - Maalle Arna Share Company
Website

ማሌ ዓርና አክሲዮን ማኅበር - Maalle Arna Share Company ወንድማማችነትና ኅብረት ለጋራ ብልጽግና

13/02/2026
ማሌ ዓርና አክሲዮን ማኅበር – 6ኛውን መደበኛ የባለ አክሲዮኖች ስብሰባበን በዛሬው ዕለት አካሄደዋል። (የካቲት 6/2018፣ ኮይቤ)በዛሬው ዕለት የማሌ ዓርና አክሲዮን ማኅበር 6ኛውን የባለ ...
13/02/2026

ማሌ ዓርና አክሲዮን ማኅበር – 6ኛውን መደበኛ የባለ አክሲዮኖች ስብሰባበን በዛሬው ዕለት አካሄደዋል። (የካቲት 6/2018፣ ኮይቤ)

በዛሬው ዕለት የማሌ ዓርና አክሲዮን ማኅበር 6ኛውን የባለ አክሲዮኖች መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤውን በአክሲዮን ማኅበሩ ጽ/ቤት ኮይቤ አካሄደዋል። የአክሲዮን ማኅበሩን ጠቅላላ ጉባዔ ባለ አክሲዮኖችን እንኳን ደህና መጣችሁ በማለት ንግግር ካደረጉ በኋላ የአክሲዮን ማኅበሩ ፕሬዝዳንት አቶ ዮሐንስ ግጬ
በይፋ መደበኛ ጉባዔውን ከፍቷል።

ለዕለቱ የተያዙ አጀንዳዎች በሙሉ ድምጽ ከፀደቁ በ2018 ዓ.ም የመጀመሪያ ስድስት ወራት የዕቅድ አፈጻጸም እና ፋይናንሻል ሪፖርት በአክሲዮን ማኅበሩ ሥራ አስኪያጅ በአቶ አቀፋ አየለ ቀርቧል።

✅ በቀረበው የ2018 ዓመት የመጀመሪያ ግማሽ አመት የዕቅድ አፈፃፀምየዕቅድ እና ፋያናንሺያል ሪፖርቱ ላይ የጉባኤ ተሳታፊዎች አስተያየት እና ጥያቄ ካቀረቡ በኋላ ሪፖርቱን በሙሉ ድምጽ አጽድቀዋል።

የአክሲዮን ማኅበሩ የውሎ አበል አሰራር ላይ ጠቅላላ ጉባኤው መሆን ባለበት ዙሪያ አቅጣጫ አስቀምጧል። የአክሲዮን ክፍያ ውዝፍ ያለባቸው በአስቸኳይ እንዲጨርሱ ውሳኔ ተላልፏል።

የመደበኛ አክሲዮን ሺያጭ በይፋ የተጀመረ በመሆኑ ቀጣይ ላይ ሁሉም ባለ አክሲዮኖች እና የሚመለከታቸው አካላት በማስተዋወቅ እና አባላትን በመሳብ ሥራ እንዲሰራ አቅጣጫ ተቀምጧል።

የማሌ ዓርና ስማርት ሲስተም Maale Arna Smart System አዲስ ፕላትፎርም የማስጀመሪያ መርሃግብር ተካሄዷል፤ ይህም የአፈፃፀምን ጥራት ለማሻሻል፣ ግልጽነትን ለማጠናከር እና የአክሲዮን ባለቤቶች እምነትን ለማጠናከር በታሳቢነት የተዘጋጀ የዲጅታል መሠረት ነው።

👏 አክሲዮን ባለቤቶች በግልጽና በትክክል የሚያመራ አቅጣጫ ሰጡ፣ ይህም ኩባንያውን ወደ ትኩረት ያለው እድገትና ኢኖቬሽን ያመራል።

አብረን ለማሌ ዓርና ብሩህና ብልህ መጻኢ ዕድልን እንገነባ! 🌟

በእርቁ በጣም ደስ ብሎናል።
07/02/2026

በእርቁ በጣም ደስ ብሎናል።

Address

Koybe
Malle

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ማሌ ዓርና አክሲዮን ማኅበር - Maalle Arna Share Company posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share

Category